About Us

ባለው የዴሞክራሲ መዋቅር እንጠቀምበት!!


የሰው ልጅ የእድገት ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ ማደጉ የተፈጥሮ ሂደት ሲሆን የእድገቱ መለኪያ ደግሞ አካላዊ ለውጥ ብቻ ሳይሆን አዕምሯዊ ወይም መንፈሳዊ ነው። ማረጋገጫው ከራሱ አልፎ ሰውን በሰውነቱ አይቶ ደስታና መከራውን በተቻለው መጠን መጋራት ሲችል ነው። ይህ የሚጀምረው ከወገኑ ሲሆን ለጥንካሬው ደግሞ አንድነቱ ወሳኝ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም። መሰባሰብ፣ መወያየትና የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መስማማት አንድነቱን እያጠነከረ ሂዶ ብዙ ጠቃሚ ሥራዎችን በጋራ ለመሥራት ያስችላል።

በስዊድን መዲና ስቶኮልም በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተሰማርተን የምንኖር ኢትዮጵያውያን ባለንበትም ይሁን በሀገራችን እየተባባሰ የመጣው አጠቃላይ ቀውስ ከማንም በላይ እንደሚያሳስበን ጥርጥር የለውም። ነገር ግን ለችግሩ መፍትሔ ለመፈለግ የምንወስዳቸው የተናጠልም ሆነ የቡድን እርምጃዎች የፈጠሩት ተፅዕኖ ጎልቶ የሚታይ አልሆነም። ስለሆነም ያለንበት አካባቢ የፈጠረልንን አመቺ ሁኔታ በመጠቀም ከወዲሁ በመደራጀት በሀገራችን ፍትሕ፣ እኩልነት፣ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ለማድረግ የበኩላችንን ማድረግ እንችል ዘንድ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራት ማሕበር ሰፊ ዝግጅት አድርጎ እየጠበቀን በመሆኑ ለሁሉም ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ጥሪውን ሲያስተላልፍ በታላቅ ደስታ ነው።


የበለጠ መረጃ ለማግኘት በሰልክ ቁጥር 0700622182 ወይም 08/911100 ይደውሉ።

እንዲሁም በኢሜይል ethio.demokrater@yahoo.com ይጻፉልን በቂ ማብራሪያ ያገኛሉ።

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራት ማሕበር

Tel. +467006221820

Box 2058

19502 Stockholm

ethio.demokrater@yahoo.com

መልእክቱን ላልሰሙ ያስተላልፉ!!

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራት ማሕበር

የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ